29 DECEMBER 2020
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የ2020 ሥራ ክንዉን | EDTF 2020 Status Update
*** Please scroll down for the English translation of this message. ***
29 DECEMBER 2020
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የ2020 ሥራ ክንዉን | EDTF 2020 Status Update
*** Please scroll down for the English translation of this message. ***
የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት አብረን እንሰራለን
እ.ኤ.አ.ነሐሴ 9 ቀን 2018 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት፤ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ከኢትዮጵያዉያን ጋር አብሮ የመስራት ተልዕኮዉን ለማራመድ ገለልተኛ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት አዋቅሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎችን በአላማዉ ዙርያ በማሰባሰብ ስራዉን በማከናወን ላይ ይገኛል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ካከናወናቸዉ በዋነኛነት ከሚጠቀሱት ተግባራት ውስጥ፤ ከ93 ሀገሮች፣ ከ26,000 በላይ ለጋሾች በማሰባሰብ፣ 48 የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ምዕራፎችን በማቋቋም፣ እና በተለያዩ መስኮች የሚያገለግሉ ከ200 በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሰባሰብ እስካሁን ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ መሰብሰብ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ፕሮጀክቶችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታዎችን መለየት፣ ፋይናንስ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ሂደት መዘርጋት፣ እና በዚሁ መሠረት ወደ ሥራ መሰማራት ይገኙበታል።
በዚህ ባሳለፍነዉ ዓመት አላማችንን ለማሳካት እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድን ራዕይ ትዉልድ ተሻጋሪነት ለማረጋገጥ ያላሰለሰ ጥረት እያደረግን ሲሆን ከለጋሾቻችን እና ደጋፊዎቻችን ጋር ሆነን ካከናወንናቸዉ ቁልፍ ተግባራት ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፤
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድን ራዕይ ለማሳካት ለሚያሳዩት ቁርጠኝነት በመላው የስራ አመራር ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርብልዎታለን። አሁንም፣ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ይህ ጉዞ በእርስዎ ቸርነት እና ያላሰለሰ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ድጋፍዎ እንዳይለየን በአክብሮት እንጠይቃለን።
መልካም አዲስ አመት!
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ
24 DECEMBER 2020
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የህክምና ዕርዳታ ፈንድ | EDTF MEDICAL RELIEF FUND
*** Please scroll down for the English translation of this message. ***
ውድ የኢዲቲኤፍ ቤተሰብ አባል እና ለጋሽ፣
ይህ መልዕክት በመልካም ጤና ላይ ሆነዉ ከፊታችን ያሉትን በአላት፣ በተለይም አዲሱን አመት፣ በተስፋ ለመቀበል በሚዘጋጁበት ጊዜ ላይ እንደደረስዎት እናምናለን። የገና በዓል እና አዲሱ ዓመት የመስጠት እና የመካፈል ጊዜ መሆናቸውን በመገንዘብ እኛም የአመቱ ማጠቃለያ የሆነዉን ትልቅ የመስጠት አስደሳች ዜና ይዘንልዎት መጥተናል።
ኢዲቲኤፍ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉትን አስቸኳይ ፍላጎቶች በጥልቅ ከመረመረ እና ከመከረ በኋላ የህክምና ተቋማትን ለማገዝ እና ለህይወት አድን የሕክምና ቁሳቁሶች መግዣ የሚዉል የአምስት መቶ ሺህ ዶላር ($500,000) የሕክምና እርዳታ ፈንድ (Medical Relief Fund) አቋቁሟል። ተጨማሪ አምስት መቶ ሺህ ዶላር ($500,000) ለማሰባሰብ የሕክምና እርዳታ ዘመቻዉን እንዲቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በእርስዎ ቸርነት ላይ በመተማመን ይህንን ፈንድ ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር ($1,000,000) እንድምናሳድግ እምነታችን ነዉ። ለዚሁ ዓላማ ተብሎ በተከፈተዉ የሕክምና እርዳታ ፈንድ (Medical Relief Fund) የልገሳ መስኮት ተጠቅመዉ የበኩልዎን ችሮታ እንዲያደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ኢዲቲኤፍ በተለያዩ ጊዜያቶች ባደረገዉ እገዛ የታመነ የኢትዮጵያ አጋር መሆኑን አረጋግጧል። አሁንም በዚህ የበዓል ሰሞን በመሰረታዊ የህክምና እርዳታ እጦት ህይወታቸዉ አደጋ ላይ የወደቀዉን ወገኖቻችንን በማሰብ እጅ ለእጅ ተያይዘን የተለመደዉን ድጋፋችንን እንድናደርግ ከአደራ ጭምር እንጠይቃለን።
መልካም የገና በዓል! መልካም አዲስ አመት!!
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ
19 MAY 2020
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ መልእክት ለለጋሾቻችን | EDTF IMPORTANT MESSAGE TO OUR VALUED DONORS
*** Please scroll down for the English translation of this message. ***
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ደጋፊዎች እና ቤተሰቦች፣
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የተሰጠውን አደራ ተቀብሎ ውጥን የልማት ሥራዎቹን ለማስጀመር እና የገጠመንን ያልታሰበ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን ላይ ሊያመጣ ከሚችለው ጉዳት ሕዝባችንን ለመታደግ ሙሉ ጊዜውን እና እውቀቱን በመስጠት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ደፋ ቀና በሚልበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ትረስት ፈንዱ የሰበሰበውን ገንዘብ አላግባብ ጥቅም ላይ አውሎ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም የተሳሳተ ዘገባ መቅረቡ በእጅጉ አሳዝኖናል።
ውድ ለጋሾቻችን !
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የተሰበሰበው ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል ለማድረግ ብክነትን፣ ገንዘብን አለአግባብ መጠቀምንና ስርቆትን ለመከላከል እና ለማመላከት የሚያስችል የአሠራር እና የመቆጣጠርያ ስልት በማበጀት የሚንቀሳቀስ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነትን መርሁ ያደረገ ተቋም ነዉ። ለወደፊቱም በዚሁ ዓላማዉ ጸንቶ የሚቆም መሆኑን ለባለድርሻ አካላት እያረጋገጥን እስከዛሬ ድረስ ምንም አይነት ገንዘብ አላግባብ ጥቅም ላይ እንዳልዋለ ልንገልፅላችሁ እንወዳለን።
በዚህ አጋጣሚ በመገናኛ ብዙኃን ስለተነሱት አንዳንድ ጉዳዮች እውነታዉን በአጭሩ እንደሚከተለው እናስገንዝብዎ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ነሐሴ 2 ቀን 2010 ዓ.ም. መቋቋሙ ይታወሳል። ይህ ቀን ዳያስፖራው ሀገር ቤት ላሉ ወገኖቹ በወል አለኝታነቱን የገለፀበት እና በረዥሙ ታሪካችን ዉስጥ በፋና ወጊነቱ ሲዘከር የሚኖር ነዉ። ትረስት ፈንዱ ምንም አይነት ልዩነት ሳያደርግ በመላዉ ዓለም ያሉትን የዳያስፖራ አባላት የአላማዉ አጋር በማድረግ ወገኖቻችንን ለመርዳት ትልቅ ራዕይ የሰነቀ ተቋም ነው።
በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶችን ለማገዝ እና በሀገራችን ውስጥ አስፈላጊ የህክምና መሳሪያዎችን እና እንደየአስፈላጊነት ሌሎች ቁሳቁሶችንም ለማቅረብ የምናደርገው ተጨማሪ መዋጮ ወገናችንን እንደሚደግፍ ሙሉ እምነት አለን።
የተከበራችሁ የባለድርሻ አካላት እና የዳያስፖራው ማህበረሰብ በሙሉ!
ወገኖቻችንን ለመርዳት ዓለም አቀፋዊ ጥረታችንን ስለተቀላቀሉ ከልብ እያመሰገንን፤ ከሁሉም በላይ ታማኝነት እና ግልፅነት የትረስት ፈንዱ የማይናወጥ ልዩ መገለጫችን እና የመርሀችን ምሰሶ መሆኑን በድጋሚ እናረጋግጣለን።
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ